(ቀን 28/03/2017 ዓ.ም) ለልመምደድ በእድገት ጮራ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሒሳብና እግሊዘኛ ትምህርት ማጎልበቻ እስትራቴጂ እና ሪፎርም አተገባበር ላይ ያለውን ምርጥ ተሞክሮ በክፍለ ከተማው ውስጥ ለሚገኙ የመንግስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አካፍሏል።
የልምድ ልውውጡ አላማ በትምህርት ቤቶች መካከል ተቀራራቢ አፈፃፀም ለማምጣት ያለመ እንደሆነም በወቅቱ ተጠቁሟል።
በዚህ የልምድ ልውውጥ የተገኙት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ለሊስቱ ተስፋዬ እንዳሉት ልምድ ልውውጥ ማድረጉ በዋናነት ራስ ጋር የሌለውን ተግባር ወደ ራስ በመውሰድ የተሻለ አፈፃፀም ማምጣትና ለውጤታማነቱ ደግሞ ተቀናጅቶ መስራት እንደሚያስፈልግ ለማሳየትና ተቀራራቢ አፈፃፀም እንዲኖራቸው ለማስቻል ነው ብለዋል።