የእድገት ጮራ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የእድገት ጮራ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዛሬው እለት ከ42 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በትህምርት ቤቱ ለመማር ማስተማሩ ሂደት እጅግ ወሳኝ የሆኑ የቤተ- መፅሐፍት ቤት፣3 የሳይንስ ላብራቶሪዎች እንዲሁም 2 የአይ ሲ ቲ ክፍሎች በበጎ ፍቃደኝነት ገንብቶ ለትምህርት ተቋሙ ያስረከበው የቲ ኤን ቲ ኮንስትራክሽን የምስጋናና የእውቅና መርሀ ግብር አካሄዷል።
በዚህ የእውቅናና የምስጋና መርሀ ግብር ላይ የተገኙት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ለሊስቱ ተስፋዬ የትምህርት ተቋማት ግንባታን ማካሄድ የመንግስት ተግባር ብቻ ሳይሆን የበጎ ፍቃደኛ ባለሀብቶች የጋራ ጥረትንና ትብብርን በመሆኑ ለነገው ትውልድ በማሠብ እንዲህን አይነት ተግባር ለፈፀም ቲ ኤን ቲ ኮንስትራክሽን ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን በቀጣይም እንዲህ አይነት ትብብር እንዳይልም ጥሪ አቅርበዋል።
በመጨረሻም በትምህርት ቤቱ የላቀ አገልግሎት ላበረከቱና በጡረታ ለተገለሉ መምህራንም እውቅና ተበርክቷል።